ለድርጅቶች

የቡድንዎ ጉዞ፣ በአንድ ሒሳብ

ሠራተኞች ይጓዛሉ፤ እርስዎ በወር መጨረሻ አንድ ሒሳብ ያገኛሉ። ማን ምን ያህል እንደሚያወጣ እርስዎ ይወስናሉ።

ለምን በድርጅት ሒሳብ

ደረሰኝ መሰብሰብ ይቀራል

ሠራተኞች በኪሳቸው አይከፍሉም፤ እርስዎም በወር መጨረሻ ወረቀት አይቆጥሩም።

ለእያንዳንዱ ሰው ገደብ

ለእያንዳንዱ ሠራተኛ ወርሃዊ ገደብ ያስቀምጡ። ሲጠጋ ያያሉ።

የተያዘው ሲፈጸም ነው

ክፍያ የሚመዘገበው ጉዞው ሲከፈል ነው እንጂ ሲያዝ አይደለም። የተሰረዘ ጉዞ ምንም አያስከፍልም።

ጉዞዎቹ በሙሉ ይታያሉ

ማን፣ መቼ፣ ከየት ወደ የትና ምን ያህል። ወርሃዊው ሒሳብ ከኋላው ዝርዝር አለው።

ጉዞ ብቻ አይደለም

ሰነድ ማድረስም በዚያው ሒሳብ ላይ ይሄዳል።

ማን እንደሚያስተዳድር ይምረጡ

ሒሳቡን የሚያየውና የሚቀይረው የተለያዩ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

እንዴት እንደሚጀመር

  1. ያነጋግሩን

    ስንት ሰዎች፣ ምን ዓይነት ጉዞ።

  2. ሒሳቡ ይከፈታል

    ወርሃዊ ገደብና የክፍያ ውል።

  3. ሠራተኞችን ይጨምሩ

    በስልክ ቁጥር። ቀድሞ የደርሳ ሒሳብ ሊኖራቸው ይገባል።

  4. በየወሩ አንድ ሒሳብ

    ከኋላው ሁሉም ጉዞዎች።