ከደርሳ ጋር ያግኙ
ተሽከርካሪዎች አሉዎት?
አንድ ባጃጅ ይሁን ሃያ — ተሽከርካሪዎችዎንና ሾፌሮችዎን ወደ ደርሳ ማስገባት ይችላሉ። ድርሻዎ በእያንዳንዱ ሥራ ላይ ይመዘገባል።
እንዴት እንደሚሰራ
ፍሊትዎን ያስመዝግቡ
እርስዎና ተሽከርካሪዎችዎ። ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ሊብሬና መድን።
ሾፌር ይመድባሉ
ሾፌሩ የራሱን ማመልከቻ ያቀርባል — በእርስዎ ሥር ሳይሆን። ማንነቱን ደርሳ ያረጋግጣል።
ድርሻውን ይስማማሉ
ሾፌሩ ምን ያህል እንደሚያስቀር አስቀድሞ ይወሰናል። ከሥራው በኋላ የሚደረግ ድርድር የለም።
ገቢው ይከፋፈላል
እያንዳንዱ የተጠናቀቀ ሥራ ለሁለታችሁም በተናጠል ይመዘገባል። ከሾፌሩ ገንዘብ መሰብሰብ የለብዎትም።
ለምን በተናጠል እንመዘግባለን
ገንዘቡ ለሾፌሩ ተከፍሎ እሱ ለእርስዎ እንዲያስረክብ ቢደረግ፣ እርስዎ የሾፌርዎ አበዳሪ ይሆናሉ። ይህ ደግሞ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የማይሠራ ዝግጅት ነው።
ስለዚህ ደርሳ ለእርስዎ የሚገባውን በቀጥታ ለእርስዎ ይመዘግባል። ክፍፍሉ ከምድቡ ጋር የተያያዘ ስለሆነ፣ ሾፌርዎ በራሱ ተሽከርካሪ የሠራው ሥራ ለእርስዎ ምንም አያስገባም — ይህም ትክክል ነው።
ማን ምን ያያል
በተሽከርካሪዎችዎ ላይ የተሠራውን ሥራና የሚገባዎትን ያያሉ። የሾፌርዎን የግል መረጃ ወይም በሌላ ቦታ የሠራውን አያዩም።
